የወሎ ዮኒቨርሲቲ ተተኪ አትሌቶችን በማፍራት በኩል ትልቅ ሚና እየተወጣ ነው፡፡ (የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን)

የወሎ ዮኒቨርሲቲ ተተኪ አትሌቶችን በማፍራት በኩል ትልቅ ሚና እየተወጣ ነው፡፡ (የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን)
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ ግንኝነት ዳሬክተር ጽ/ቤት (መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም)
ይህ የተባለው በኮሎምቢያ ካሊ ከተማ በተደረገው የአለም ታዳጊዎች ሻምፒዮና ላይ ተሳትፍ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ ላመጣችው አትሌት ጽዮን አበበ እውቅና በተሰጠበት ወቅት ነው።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ስራ አሰፈጻሚና ተቀዳሚ ምክትል ኘሬዝዳንት ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በኦሪገን እና በኮሎምቢያ በተደረጉ አለም አቀፍ ውድድሮች ከስከዛሬው በተሻለ መልኩ ውጤት መገኘቱን የገለጹ ሲሆን በዚህም በወሎ ዮኒቨርሲቲ የሚመራው ተንታ አትሌቲክስ ማእከል የተሻለ ተሳትፎ ነበረው ብለዋል።
ፌደሬሽኑ በስልጠናው ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግና ማእከሉ ተተኪዎችን በተሻለ መንገድ እንዲያፈራ በማድረግ በኩል ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የወሎ ዮኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ በበኩላቸው አትሌቷ ላመጣችው ውጤት አመስግነው ዮኒቨርሲቲው በቀጣይ ተንታ አትሌትክስ ማእከል የተሻለ እንዲሆን 50 ሚሊዮን ብር በመመደብ ከ50 በላይ አትሌቶችን ለማፍራት እየሰራ መሆኑን ገልጠዋል፡፡
ኘሬዝዳንቱ አክለውም ማእከሉ በአለም አቀፍ መድረኮችና በተለያዮ የሀገር ውሰጥ ውድድሮች 13 ወርቆችን እንዲሁም ብርና ነሀስን ጨምሮ በጥቅሉ 49 ሜዳሊያዎችን ማምጣቱን ገልጸው ወደፌትም ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት ይሰራል ብለዋል።
እውቅና እና ማበረታቻ የተሰጣት አትሌት ጽዮን አበበ በበኩሏ ከዚህ በበለጠ በመስራት ለሀገሯ የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንደምትስራ ተናግራለች። ለአትሌቷ የ150 ሺህ ብር ቤት ውስጥ ቁሳቁስ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ 50 ሽህ ብር ከተንታ ወረዳ እና የቤት መስሪያ ቦታ ከኮምቦልቻ ከተማ አስተደደር ድጋፍ ተደርጎላታል።
በእውቅና ኘሮግራሙ ላይ የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝና የደሴና የደቡብ ወሎ ዞን አመራሮች፣ የአብክመ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

Scroll to Top