የመምህራን ስነ ባህሪ ተቋም 3ኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ እያካሄደ ነው

ሰኔ 1/2015 ዓ ም (ወሎ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጽ/ቤት)

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የመምህራን ስነ ባህሪ ተቋም” Education for Social Reconstraction” በሚል መሪ ቃል ሶስተኛውን ሀገራዊ የምርምር ኮንፍረንስ እያካሄደ ነው።

የኮንፍረንሱን ተሳታፊዎችና ምርምር አቅራቢዎች እንኳን በሰላም መጣችሁ ያሉት የተቋሙ ዲን ዶ/ር ጌታቸው ጣሰው ትምህርት በሁሉም አቅጣጫ ለሚደረገው ለውጥና እድገት መነሻ በመሆኑ በጥናት ላይ የተደገፉ ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንሶችን ማካሄድ ወሳኝ ነው ብለዋል።

በዚህ የምርምር ኮንፍረንስ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ያሉብንን የውስጥ ተግዳሮቶች በመፍታት ሀገራዊ እድገትንና አንድነትን ለማምጣት የዘርፉ ምሁራንና ተመራማሪዎች ትምህርትን ለማህበረሰብ ግንባታ ማዋል ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

አያይዘውም ፕሬዚዳንቱ ሀገራዊ ኮንፍረንሱ የሀገራችንን የትምህርት ቤት፣ የመምህራንና የትምህርት ሀብት ሊያሻሽል በሚያስችል መልኩ ጥናቶች እንዲካሄዱ አሳስበዋል።

በኮንፍረንሱ ትምህርት ለሀገርና ማህበረሰብ ግንባታ ያለውን ፋይዳ የሚገልጽ ቁልፍ ንግግር በፕሮፌሰር ሀብታሙ ወንድሙ፣ ዶ/ር ዳዊት መኮነንና ዶ/ር መስከረም ለጪሳ ተደርጓል።

በዚህ የትምህርት ሀገር አቀፍ ኮንፍረንስ ላይ 8 (ስምንት) ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው ይሆናል።

ኮንፍረንሱም ከሰኔ1-2/2015 ዓ ም ለተከታታይ ሁለት ቀን ይካሄዳል።

Scroll to Top