የሃዘን መግለጫ

ነሃሴ 10 ቀን 2014 ዓ. ም (ወዩ ህ/ ግንኙነት ዳይሬክተር ጽ/ቤት)

ተማሪ ሙባረክ ሰይድ ሁሴን ነሃሴ 8 ቀን 2014 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ደሴ ከተማ ባንቧ ውሃ አካባቢ በደረሰበት ድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል። ተማሪው በደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ገብቶ ላለፉት ሁለት ቀናት ህክምና ቢደረግለትም የጉዳቱ መጠን ከፍተኛ ስለነበር ህይወቱን ማትረፍ ሳይቻል ቀርቷል።

ተማሪ ሙባረክ የ1ኛ አመት ተማሪ የነበረና ክረምቱን ትምህርቱን በመከታተል ላይ ነበረ። አስከሬኑ ቤተሰቦቹ ወደሚገኙበት ደሴ ከተማ አቅራቢያ ወደሚገኘው ቆርኬ አካባቢ ተሸኝቶ በዛሬው ዕለት ነሃሴ 10/2014 ዓ.ም የቀብር ስርዓቱ ተፈጽሟል።

ፈጣሪ የተማሪውን ነብስ በአፀደ ገነት እንዲያኖርልን እየተመኘን ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለክፍል ጓደኞቹ መጽናናትን እንመኛለን።

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የህ/ግንኙነት ዳይሬክተር ጽ/ቤት

Scroll to Top