ወሎ ዩኒቨርሲቲ “Change and change management in time of Crisis” በሚል መሪ ቃል ሲሚናር አካሄደ

መጋቢት 13/2016 ዓ ም (ወዩ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጽ/ቤት)

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የቢዝናስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ለውጥና የለውጥ አመራር ላይ ያተኮረ ሲሚናር አካሄዷል።

በሲሚናሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ወሎ ዩኒቨርሲቲ በሰሜኑ ጦርነት ያጋጠመውን መከራ በለውጥ አመራሩ ተግባቦትና ውሳኔ የተሻለ ለውጥ ለማምጣች እንደት እንደቻሉ በመግለጽ እንድህ አይነት ሲሚናር መካሄዱ በቀውስ ወቅት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት መነሻ ሀሳብ የሚያስጨብጥ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የተካሄደው ሲሚናር ለውጥና የለውጥ አመራሩ የሚያጋጥሙ ቀውሶችን እንደት አድርገው በማስተዳደር ወደ ለውጥ መቀየር እንደሚችሉ ሀሳብ የተንሸራሸረበት ነው ያሉት የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ይመር አያሌው ተመሳሳይ ሲሚናሮችን በማዘጋጀት ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት ኮሌጁ ይሰራል ብለዋል።

በሲሚናሩም “Organizational and its change management in time of Crisis” በሚል ርዕስ በማኔጅመንት ትምህርት ክፍል መምህር ሙሉጌታ ጫኔ የመነሻ ጽሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሄዶበታል።

Scroll to Top