ወሎ ዩኒቨርሲቲ የአርት ት/ቤቱን መልሶ ለመገንባት ከUSAID ጋር በትብብር መልሶ ለመገንባት እየሰራ ነው።

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የልጅ እያሱ የሰላምና ዲሞክራሲ የምርምር ተቋም ከUSAID አለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር አርትን ለሰላም እሴት ግንባታ ለማዋል እየሰራ ነው።

የዩኒቨርሲቲው የምርምር ተቋም ከአለም አቀፉ የUSAID ድርጅት ጋር በፈጠረው የፕሮጀክት ግንኙነት በህወሀት ወራሪው ሀይል የወደመበትን የአርት ት/ቤት መልሶ ለመግንባት የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

በፕሮጀክት ትውውቁ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ የልጅ እያሱ የሰላምና ዲሞክራሲ የምርምር ተቋም በወራሪ ሀይሉ የተመዘበረውን የሙዚቃና ትያትር ት/ክፍሎች መልሶ በመገንባት የዩኒቨርሲቲውን የባህልና የኪና ጥበብ የልህቀት ማዕከል እውን ለማድረግ የሰራው ስራ ሊያስመሰግነው ይገባል ብለዋል።

አያይዘውም ፕሬዚዳንቱ የአርት ትምህርት ቤቱ በዩኒቨርሲቲውና በUSAID ድጋፍ የሚገነባውን ዘመናዊ የሙዚቃ ስቲድዮ እና የትያትር መድረክ (stage) አቅምን አሟጦ በመጠቀም በወሎ ያለውን ኪነ ጥበብ ለሰላም እሴት ግንባታ መጠቀም ተገቢ ነው ብለዋል።

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የልጅ እያሱ የሰላምና ዲሞክራሲ የምርምር ተቋም ባቀረበው ፕሮጀክት መሰረት የዩኒቨርሲቲውን የአርት ት/ቤት መልሶ በመገንባት ለሰላም እሴት ግንባታ ለማዋል USAID 10 ሚሊዮን ብር በጅቷል ያሉት የምስራቅ አማራ USAID ተወካይ አቶ ዳንኤል አሰፋ ድርጅቱ ደረጃውን የጠበቀ የሙዚቃ ስቲድዮና የትያትር መድረክ ለመገንባት ሙሉ ቁሳቁሶችን ከአሜሪካን ሀገር ግዥ እንደሚፈጽሙ ተናግረዋል።

በፕሮጀክት ትውውቁ ላይ የተሳተፉት የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት፣ የማህበራዊና ሰብዓዊ ሳይንስ ኮሌጅ ተወካይ፣ የአርት ት/ቤት መምህራንና ተመራማሪዎች የልጅ እያሱ የሰላምና ዲሞክራሲ የምርምር ተቋም ለሰራው መልካም ተግባር ያላቸውን አድናቆት በመግለጽ በወሎ ያለውን እምቅ አርት አውጥቶ ለመጠቀም ጊዜው አሁን ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

Scroll to Top