ሐምሌ 28/2014 ዓ.ም (ወ.ዩ. ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጽ/ቤት)
ወሎ ዩዩቨርሲቲ ከባንኮች ጋር አብሮ ለመስራት ለሁሉም የግል ንግድ ባንኮች ባቀረበው ግብዣ መሰረት አዋሽ ባንክ የተሻለ የአገልግሎትና የብድር ምጣኔ በማቅረቡ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ውል ስምምነት ተፈራርመዋል።
ባንኩ በተመጣጣኝ የወለድ ምጣኔ የባንክ አገልግሎቶችን ለዩኒቨርሲቲውና ለሰራተኞቹ ቀላል፣ ቀልጣፋና ሰፊ ተደራሽነት ባለው መልኩ ለመስጠት የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ስምምነቱን ተፈራርሟል።
ስምምነቱን የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ እና የአዋሽ ባንክ ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ ድስትሪክት ኃላፊ አቶ ኤልያስ እሸቱ ተፈራርመዋል።