ወሎ ዩኒቨርሲቲ አለም አቀፍ የደን ቀንን “Forest and Innovation: New solution for a better Word” በሚል መሪ ቃል አከበረ።

መጋቢት 11/2016 ዓ ም (ወሎ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጽ/ቤት)

በየዓመቱ በአለም የሚከበረውን የደን ቀን ምክንያት በማድረግ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የደን ትምህርት ክፍል በዩኒቨርሲቲው ለ9ኛ ጊዜ አለም አቀፍ የደን ቀንን አክብሯል።

ይህንን አለም አቀፍ የደን ቀን ምክንያት በማድረግ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ በዘርፉ ያሉ ምሁራን በሀገራችን ሳይንሳዊና ዘላቂ የደን ልማት እንዲኖር በማድረግ ለሰው ልጅ ተስማሚና ምቹ አለም እንዲፈጠር የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል።

በእለቱም በኢትዮጵያ ዘላቂ የደን ልማት ለማምጣት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ምሁራን ቁልፍ ንግግር አድርገዋል።

በዚህ አለም አቀፍ የደን ቀን የኢትዮጵያ ደን ልማት፣ የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ፣ የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ፣ የአለም ምግብ ፕሮግራም፣ የወሎ ዩኒቨርሲቲና ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የመወያያ ጽሁፍ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተካሄዶበታል።

Scroll to Top