ወሎ ዩኒቨርሲቲ በደሴ ከተማ ለሚገኙ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ተፈታኝ ተማሪዎች የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት እንደ አንድ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራ ለመስጠት ከደሴ ከተማ ትምህርት መምሪያ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በደሴ ከተማ ለሚገኙ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ተፈታኝ ተማሪዎች የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት እንደ አንድ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራ ለመስጠት ከደሴ ከተማ ትምህርት መምሪያ ጋር በጋራ ለመስራት በመስማማት በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ያለውን ክፍተት ለማጥናት በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት የሚመራ ቡድን ከተለያዩ የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራንና ተማሪዎች ጋር በቦታው ላይ በመገኘት ከተወያየ ብኋላ በተለዩት ክፍተቶች ላይ ምሁራንንና ለስራው የሚውል በጀት በመመደብ ለማሟላት ቃል በመግባት ስራዉን ጀምሯል፡፡

Scroll to Top