ነሐሴ 13 ቀን 2014 ዓ.ም (ወዩ ህ/ግንኙነት ዳይሬክተር ጽ/ቤት)
የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ነሐሴ 12/2014 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ እስከ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም በኮሌጅ የአካዳሚክ ኮሚሽን ታይቶ እንዲጸድቅላቸው ለሴኔት በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ መሰረት ለ24 መምህራን የአካዳሚክ ደረጃ እድገት ሰጥቷል::
የአካዳሚክ ደረጃ እድገት ከተሰጣቸው 24 መምህራን ውስጥ 21 መምህራን የረዳት ፕሮፌስርነት ማዕረግ ሲሆን 3 መምህራን ደግሞ የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ነው፡፡
የተባባሪ ፕሮፌስርነት ማዕረግ የተሰጣቸውም፡-
1. ዶ/ር መታደል አዳነ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን እና የዩኒቨርሲቲው የአቢሲኒያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጆርናል ዋና ኤዲተር ሲሆኑ ከ40 በላይ የምርምር ህትመት ስራቸውን በማቅረብ፣
2. ዶ/ር ሰይድ ጌታሁን 14 የምርምር ህትመት ውጤቶችን በማቅረብ፣ በህክምና ሙያቸው ከፍተኛ የማህበረሰብ አገልግሎት በማበርከት፣ የውጭ ፕሮጀክት በማምጣት ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረግና ሌሎች ለደረጃ እድገቱ የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን በማሟላታቸው ፈጣን ዕድገት (accelerated promotion) የተሰጣቸው
3. ዶ/ር የሱፍ አህመድ በህክምና ት/ቤት ውስጥ የጽንና ማሕፀን ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም የሆኑ 10 የምርምር ህትመት ውጤቶችን በማቅረብና ለበርካት አመታት በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት በመስራታቸው ማዕረጉ ተሰጥቷቸዋል፡፡
በዚሁ አጋጣሚ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በምሁራኑ ዕድገት የተሰማውን ደስታና አድናቆት ገልጿል፡፡