ግንቦት 25/2015 ዓ ም ( ወሎ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጽ/ቤት)
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ህግ ት/ቤት ከፌደራል ፍትህ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ለማስከበርና ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት የሚያስችል ሀገራዊ የምክክር ኮንፈረስ አካሄዷል።
ኮንፈረንሱን ያዘጋጀው የህግ ት/ቤት ዲን አቶ ሰለሞን ጎራው የህግ ት/ቤቱ ተማሪዎችን በማብቃት የተሻለ ስራ እየሰሩ እንደሆነ ገልጸው እስካሁን ተመርቀው የመውጫ ፈተና ከወሰዱት መካከል 96ቱን% ማሳለፍ ተችሏል።
የኮንፈረንሱን ተሳታፊዎች እንኳን ወደ ታሪካዊ ወደሆነው ወሎ በሰላም መጣችሁ ያሉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ሀገራዊ አንድነትን፣ ፍትህንና ሰላምን ለማምጣት ሀገራዊ ኮንፈረንስ ማዘጋጀት ወሳኝ ነው ብለዋል።
አያይዘውም ፕሬዚዳንቱ ኮንፍረንሱ በሀገር ደረጃ እየተካሄደ ላለው ሀገራዊ የምክክር መድረክ የራሱን አወንታዊ ሚና ይጨዋታል ብለዋል።
በዚህ ኮንፍረንስ ላይ የመክፍቻ ንግግር ያደረጉት የፌደራል ፍትህና ህግ ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ማዳ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደው የምርምር ኮንፍረንስ በሀገር ደረጃ እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ የምክክር መድረክ ለማሳለጥ የራሱን ሚና ይወጣል ሲሉ ገልጸዋል።
ከግንቦት 25-26/2015 ዓ ም እየተካሄደ ባለው የምርምር ኮንፍረንስ 8 (ስምንት) ያክል ጥናታዊ ጽሁፎች የሚቀርቡ ይሆናል።
