ሰኔ 17 ቀን 2015 ዓ.ም (ወሎ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ ህንኙነት ዳይሬክተር ጽ/ቤት)
3ኛው የኢትዮጵያ ማሰልጠኛ ማዕከላት የአትሌቲክስ ሻምፒዮኛ ከሰኔ14-17/2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የተንታ አትሌቲክስ የበላይነት ተጠናቀቀ ።በስድስት የማሰልጠኛ ማዕከላት በተካሄደው ውድድር በወሎ ይንቨርሲቲ በወንድም በሴትም በአጠቃላይ ውጤት የሶስት ዋንጫ ባለቤት ሁኗል።
በዚህም መሰረት
በሴቶች
- 183 ነጥብ በማምጣት 1ኛ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የተንታ አትሌቲክስ ማዕከል
- 163 ነጥብ በማምጣት 2ኛ የደብረ ብርሃን ማሰልጠኛ ማዕከል
- 135 ነጥብ በማምጣት የባሬ ማሰልጠኛ ማዕከል
በወንዶች - 193 ነጥብ በማምጣት በወሎ ዩኒቨርሲቲ ማሰልጠኛ ማዕከል
- 173 ነጥብ በማምጣት የሀገረሰላም ማሰልጠኛ ማዕከል
- 112 ነጥብ በማምጣት የደብረብረሃን ማሰልጠኛ ማዕከል
በአጠቃላይ ውጤት በሴትም በወንድም - 376 ነጥብ በማምጣት በወሎ ዩኒቨርሲቲ ማሰልጠኛ ማዕከል
- 275 ነጥብ በማምጣት የደብረብረሃን ማሰልጠኛ ማዕከል
- 255 ነጥብ በማምጣት ሀገረሰላም ማሰልጠኛ ማዕከል
ውጤት አምጥተዋል።
“እንኳን ደስ ያላችሁ”

