ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ( ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጽ/ቤት)
በወሎ ዩኒቨርሲቲ የስነ ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክተር ጽ/ቤትና የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክተር ጽ/ቤት በጋራ በመሆን ስነ ምግባራዊ አምራርና የሙስና መከላከያ ስልቶች አና ቅንጅታዊ አስራር ላይ ትኩረት ለሚሹ የስራ ክፍል ሰራተኞች (ለግዥና ንብረት አስተዳደር፣ ለሰው ሃብት ልማት፣ ለፋይናንስ አስተዳደር እና ለጠቅላላ አገግሎት ) ስልጠናው ተሰጥቷል።
በስልጠናው ላይ ተገኝተው ለሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፋሪስ ሀይሉ እንደተናገሩት ሙስና ለሃገርና ለተቋማዊ ዕድገት ጎጅ የተለያዩ ጉድለቶችንና የአሰራር ክፍተቶችን የሚፈጥር በመሆኑ የአስራር ክፍተቶችን ለመሙላትና የተቃና የስራ አካባቢንና ሰራተኛን ለመፍጠር በስነምግባራዊ አሰራር፣ የሙስና መከላከያ ስልቶችንና ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጠናከር ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው ሰልጣኞች ስልጠናውን ያለምንም ማቆራርጥ መከታተልና ተሳታፊ እንዲሆኑ አሳስበዋል።
ሰልጠናውን የሰጡት በማህበራዊና ሰብአዊ ሳየንስ ኮሌጅ የስነዜጋና ስነምግባር መምህርና የትምህርት ክፍል ሃላፊ አቶ አደራጀው አለም እና በዩኒቨርሲቲው የህግ አገልግሎት ዳይሬክተርና የህግ ት/ቤት መምህር አቶ ተመስገን ተሰማ (ስነ ምግባርና የሙስና ጉዳቶች ፣ የሙስና ወንጀሎችና ድንጋጌዎች) በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች የመወያያ ሰነድ ቀርበው ሰልጣኞችውይይት አድርገውበታል።
ተሳታፊዎች በውይይታቸው እንዳሳሰቡት ሁላችንም የምንሰራው ለአንድ ተቋም ለተመሳሳይ አላማ በመሆኑና ያንዱ ስኬትና ውድቀት ለሌላው መሆኑን ተገንዝበን እርስብርስ ከመፈራረጅ ፣ ከመጠላለፍ ፣ ከመወነጃጀል፣ ከመተማማትና ተቋሙን ከማብጠልጠል ተቆጥበን በጋራ ተረዳድተን፣ ተጋግዘንና በመካከር ስሜት ለተቋሙ ውጤታማነት እንትጋ ብለዋል።
በስልጠናው ማጠናቀቂያ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌትነት መልአክ በበኩላቸው የተቋሙ ሰራተኛ ሁሉም ለተቋሙ አስፈላጊ ነው ካሉ በኋላ የሰለጠናችሁትን ወደ ተግባር መቀየር አለባችሁ ሲሉ አሳስበዋል።
አቶ ጌትነት አያይዘውም ተቋሙ ውጤታማ የሚሆነው በተናጥልም ሆነ በግል በምናደርገው ጥረት በመሆኑ ምክንያታዊ ሆነን ተቋሙን ከማይመጥኑ አላስፈላጊ ድርጊቶች ተቆጥበን ለተቋማችን ውጤታማነት ተቆርቋሪ ሆነን ልንሰራ ይገባል ብለዋል
በውይይቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ከአሰልጣኞች ጋር በመሆን ማጠቃለያ የሰጡት የዩኒቨርሲቲው የስነ ምግባርና ጸረ -ሙስና ዳይሬክተር ወ/ሮ ወላንሳ ተክሌ በበኩላቸው ችግሮችን ወደሌላ ከመጠቆም ተቆጥበን የራሳችንን ክፍተት በማረም ለስራችን ቅን ታማኝ ሆነን መስራት አለብን ሲሉ አሳስበዋል በውይይቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ከአሰልጣኞች ጋር በመሆን ማጠቃለያ የሰጡት የዩኒቨርሲቲው የስነ ምግባርና ጸረ -ሙስና ዳይሬክተር ወ/ሮ ወላንሳ ተክሌ በበኩላቸው ችግሮችን ወደሌላ ከመጠቆም ተቆጥበን የራሳችንን ክፍተት በማረም ለስራችን ቅን ታማኝ ሆነን መስራት አለብን ሲሉ አሳስበዋል
