ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም (ወሎ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጽ/ቤት)
ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው የፈተና መርሃግብር መሰረት ከሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም በወሎ ዩኒቨርሲቲ በደሴና በኮምቦልቻ ግቢ ሲሰጥ የነበረው የዩኒቨርሲቲ ማጠናቀቂያ የመውጫ ፈተና (Exit examination) ዛሬ ተጠናቋል።
የዩኒቨርሲቲያችን የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አወል ሰይድ የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክክተው እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው የመውጫ ፈተናውን ለመስጠት በአደረገው ቅድመ ጥንቃቄና ዝግጅት መሰረት ያለምንም ችግር ተሰጥቶ ተጠናቋል ብለዋል።
ም/ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም የዘንድሮ የመውጫ ፈተና የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው በሁለቱም ግቢዎች (ደሴና ኮምቦልቻ) ፈተናቸውን መውሰዳቸውን ገልጸው ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ዕድል እንዲገጥማቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል።