ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከጣሊያን የቶሪኖ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር እንደሚሰራ ተገለጸ።
  December 03, 2019    News

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከጣሊያን የቶሪኖ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር እንደሚሰራ ተገለጸ። ========================== የቶሪኖ ዩኒቨርሲቲ ከአውሮፓ ባገኘው የበጀት ድጋፍ በምስራቅ አፍሪካ ካሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል። ዩኒቨርሲቲው በሀገራችን ኢትዮጵያ የከፍተኛ ት/ተቋማትን በስልጠና ፕሮግራሞች ለማገዝ 97 ሺ 348 ዩሮ ወይም 3,309,832 ብር መድቦ እየተንቀሳቀሰ ነው። በዚሁ መሰረት የቶረንቶ ዩኒቨርሲቲ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በባዮሎጅ፣ በከሚስትሪ፣ በአግሮኖሚክስና በፋርማኮሎጅ የስልጠና መስኮች በቅድመና በድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ለሶስት አመታት በትብብር ለመስራት ተስማምቷል።