በ2012 ዓ.ም ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል የወሎ ዩኒቨርሲቲ ከተማሪዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።
  October 10, 2019    News

በወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ ም በተቋሙ ያለውን ሰላማዊ የማስተማር ሂደት ለማስቀጠል መምህራንና ሰራተኞች ተማሪዎችን ተቀብለው እንዳባት እየመከሩና እየዘከሩ ሙሉ ሰው አድርገው ለማስመረቅ በመወሰን ወደ ስራ ገብተዋል ። በወሎ ዩኒቨርሲቲ ያለውን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት በማስቀጠል የተቋሙ ተማሪዎች የሰላም አምባሳደር ሁነው እንድያስቀጥሉት በሰላማዊ የመማር ማስተማር ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው። በዚህም ውይይት ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወሎ ዩኒቨርሲት ፕሬዚዳንት ዶ/ር አባተ ጌታሁን ሁሉም ነገር በሰው ልጆች ውስጥ ያለ በመሆኑ በጎውን ነገር መርጣችሁ በመዝራት አንድነትን፣ አብሮነትንና ፍቅርን በማሳደግ የሰላም አምባሳደር ሁነው እንድቀጥሉ ለተማሪዎች መልእክት በማስተላለፍ ንግግራቸውን ጀምረዋል። አያይዘውም ፕሬዚዳንቱ በተያዘው የመማር ማስተማር ዓመት የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሰራተኛች በነብስ ወከፍ ከ15 በላይ ተማሪዎችን እንደ አባትና እናት ተቀብለው እየመከሩና እየዘከሩ ሙሉ ሰው አድርገው ለማስመረቅ ቃል በመግባታቸው ተማሪዎች ልጅ ሁናችህ እንድትቀበሏቸ ሲሉ ተናግረዋል። የሀይማኖት አባቶችም በዚህ የተማሪዎች ውይይት ላይ በመገኘት ተማሪዎች ሰላምን አንድነትንና ፍቅርን በመዝራት በመንፈሳዊም ሆነ በዓለማዊ ህይወታቸው ስኬታማ እንድሆኑ አባታዊ ምክራቸውን አስተላልፈዋል። በዚህ ዓመት በወሎ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎቹ የመኝታ ክፍል ፣ የመኖሪያ ህንጻንና አካባቢን በማስረከብ ሀላፊነታቸውን እንድወጡ ይደረጋል።